MENU

Where the world comes to study the Bible

እንዴት ሀሰተኛ ነብያትን መለየት ይቻላል?

ማቴዎስ 7፡ 13-23

13 በጠበበው ደጅ ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው፤ 14 ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ፥ መንገዱም የቀጠነ ነውና፥ የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው። 15 የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።16 ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። ከእሾህ ወይን ከኩርንችትስ በለስ ይለቀማልን? 17 እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያደርጋል፥ ክፉም ዛፍ ክፉ ፍሬ ያደርጋል።18  መልካም ዛፍ ክፉ ፍሬ ማፍራት፥ ወይም ክፉ ዛፍ መልካም ፍሬ ማፍራት አይቻለውም። 19 መልካም ፍሬ የማያደርግ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል ወደ እሳትም ይጣላል። 20  ስለዚህም ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ። 21  በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። 22  በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። 23  የዚያን ጊዜም፦ ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።

ሀሰተኛ ነብያት እውነተኛ መስለው ስለሚቀርቡ በጣም አደገኛ ናቸው። የትክክለኛ የነብይነት ስጦታ እና ስልጣን እንዳላቸው አድርገው ራሳቸውን ያቀርባሉ። ይህ የሚመስሉበት ስልጣን ምንድ ነው? ኢየሱስ እንዳለው ራሳቸውን የበግ ለምድ አልብሰው ያቀርባሉ። ማቴ 7 ፡15 ይመለከቱ።

ሀሰተኛ ነቢያት የበግ ለምድ ለብሰው የሚመጡ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ናቸው ይላቸዋል። እረኛ በኮረብታማ ስፍራ መንጋውን ሲጠብቅ የበግ ለምድ ለብሶ ነው። እረኛም ያልሆነ ሰው ደግሞ የበግ ለምድ ሊለብስ እና እንደ እረኛ ሊያስመስል ይችላል። ነብያቶችም የተለመደ የአለባበስ አውድ ነበራቸው። ነብዩ ኤልያስ መጎናፀፊያ ያደርግ ነበር በዚህም ከሌሎች ይለይ ነበር። 1ኛ ነግስት 19፡13፥19 የግሪክ ፈላስፎች የራሳቸው የአለባበስ ስርዐት እንደነበራቸው ነብያትም የቆዳ መጎናፀፊያ በመልበስ ይታወቁ ነበር። ነገር ግን ይህን መለያ ልብስ ያልተገባቸው ነብያት ያልሆኑ ለብሰውት ሊገኙ ይችላሉ።ለዚህም ነው በነብዩ ዘካሪያስ 13፡4 ላይ እንዲህ የተፃፈው። “በዚያም ቀን ነቢያቱ ሁሉ ትንቢትን ሲናገሩ እያንዳንዱ ስለ ራእዩ ያፍራል ያታልሉም ዘንድ የማቅ ልብስ አይለብሱም።” ዘካሪያስ 13፡4  የነብያትን መጎናፀፊያ እየለበሱ ነብያትን የሚመስሉ ነገር ግን ፈፅመው ያሆኑ ይኖራሉ። ዊሊያም ባርስሌይ፥ የማቲዎስ ወንጌል መፅሀፍ The Gospel of Matthew (Edinburgh: The Saint Andrew Press, 1963), 1, p. 286.]

ሀሰተኛ ነብያቶች በዉጫዊው አቀራረባቸው አንዳንዶችን ያስታሉ እንደታማኝ መሪዎችም ይቆጠራሉ። ይህንንም በልዩ ልዩ አለባበስ ራሳቸውን ለየት ለማድረግ ሊሞክሩ ይችላሉ። እንዲሁም የስም ማዕረጎችን በስማቸው ላይ ይደረድራሉ። በሃይማኖት ስርዓት ዉስጥም ትልልቅ የመሪነትን ስፍራ ተቆናጠው ሊገኙ ይችላሉ። በትምህርትም የስነመለኮት ትምህርት ተምርውም ሊሆን ይችላል። አልፎም ተርፎም በስነመለኮት ትምህርት አስተማሪዎችም ሊሆኑ ይችላል። በነዚህ ሁሉ ሁነታዎች እንደ ታማኝ መሪዎች ቆጥረናቸው ከሆነ ትክክል አይደልም። በየዋህነትም በውጫዊ ማንንተቸው ድምዳሜ ላይ ልንደርስ አይገባም።

ሀሰተኛ ነብያቶች በፍሪያቸው ይታወቃሉ። በውጫዊ ማንነት ላይ ተመስርቶ መደምደም አያዋጣም፤ለዚህም ነው በፊሬያቸው መለየት እጅግ ጠቃሚ እና አስፈላጊ የሚሆነው። የዛፍ የስሩ ምንነት መታወቂያው በፍሬው ነው። መልካም ዛፍ መልካም ፍሬን ይሰጣል። መጥፎ ዛፍ እንድሁ መጥፎ ፍሬን ይሰጣል። ስለዚህም ታምኝ የሆኑ መሪዎችን የመመዘኛ መንገዱ በፍሬዎቻቸው መሆን አልበት። ማቴ 7፡20

ነገር ግን እንዚህ ፍሬዎች ታድያ ምንድን ናቸው? እዚህ ላይ ልብ ማለት ይገባል፤ሀሰተኛ ነብያቶች ሃይማኖታዊ ስርዓቶችን የማይፈፅሙ አይደሉም። ይልቁንም ሀሰተኛ ነብያቶች በሀሰተኛ ምልክቶች እና በሚመስሉ ታዓምራቶች የተሞሉ ናቸው። ይህንንም በማቴዎስ ወንጌል 7፡22 ተጠቅሰው እናገኛለን።

“በዚያ ቀን ብዙዎች፦ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።” ማቴዎስ ወንጌል 7፡22

ሀሰተኛ ነብያቶች በልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ስራ እና መሰል ተግባራትን ሊፈፅሙ ይችላሉ።

ታዓምራትን የማድረግ ሃይል አላቸው ላማስባል ልዩ ልዩ መሰል በጎ አድራጎትን ያደርጋሉ። የሚደረጉትን ታዓምራቶች በስመ እግዚአብሔር እና ለእርሱ ክብር ነው ሊባልም ይችላል።

“እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ፥ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞች ሠራተኞች ናቸውና። 14 ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና። 15 እንግዲህ አገልጋዮቹ ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።”  2 ቆሮ 11፡ 13-15

ሌላው ልብ ሊባል የሚገባው ነገር ሀሰተኛ ነብያቶች በእግዚአብሔር ስም ለየት ባለ እና አግራሞት ባለበት የሃይማኖት ስርዓቶች ሲታጀቡ ማየት ነው። ሰይጣንም ብዙዎችን እስካሳተ እና ለእርሱ ፍቃድ ሰዎችን እስካአስገዛ ድረስ ክብርን ለእግዚአብሔር መስጠት ችግሩ አይደለም።

ታድያ ጌታ የተናገረው እነዚህ የሃይማኖት ስርዓቶች ናቸው? ከላሁኑ ታድያ ምንድን ናቸው? በምንመለከተው ነገር ምንም ጥርጥር እንዳይገባን መፅሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ የሀሰተኛ ነብያትን ፍሬዎች ይገልፃል። ይንንም የሃሰተኛ ነብያት ፍሬዎች በሶስት ክፍል ልናስቀምጣቸው እንችላለን።

1. የመጀመሪያው የሀሰተኛ ነብያት ፍሬዎች ከአስተምሮ አንፃር

ሀሰተኛ ነብያት የሚናገሩት በመለኮታዊ ስልጣን ሳይሆን ከራሳቸው ከንቱ ስሜት ነው። ኤርሚያስ 23፡16፥21፡25 ህዝቄል 12፡2

 • የእግዚአብሔርን ቃል አይሰብኩም ወይም አይጠብቁም ይልቁንም ይክዱታል። ኤርሚያስ 23፡17 በተልይም ሊከሰት ይሚችል ሁነታዎች ነገር ግን ደስ ያማያሰኙ ሲሆኑ እውነታውን ይክዳሉ። ኤርሚያስ 6፡14 ፤28፡17 ህዝቄል 13፡1
 • ለልዩ አጣዳፊ እና ወቅታዊ ጉዳዩች ላይ ምላሽ በመስጠት ይታወቃሉ። ኤርሚያስ 8፡11።
 • ሰዎች በጆሮቸው ሊሰሙ የሚወዱትን ይናገራሉ። 1 ነገስት 22፡8 2 ጢሞቲዎስ 4፡3-4
 • በድነት ጉዳይ ላይ የኢየሱስ ማንነት እና ጌትነትም ይክዳሉ። በመስቀል ላይ የተከፈለውን ስራም እንዱሁ ይክዳሉ። 2 ጴጥሮስ 2፡1 1ዮሐንስ 4፡2-3

2. ሁለተኛው የሀሰተኛ ነብያት ፍሬዎች ክፍል ደግሞ ትምህርታቸው በሌሎች ላይ የሚፈጥረው ተፅዕኖ ነው።

 • በተመሳሳይ ሁነታ ትምህርቶቻቸው የሚያመራው የእግዚአብሔርን ቃል መናቅ፥
 • መፅሐፍቅዱስን ስልጣን አለመቀበል፥
 • በቅዱሳን መካከል ልዩነትን መፍጠር፥ ኤርሚያስ 23፡2፤14 ብሎም የስጋዊነት ባህሪያት ናቸው። 2ጴጥሮስ 2፡2።
 • በተቻላቸው ሁኔታ ሰዎችን ከእውነተኛ ወንጌል ለማራቅ ይጥራሉ። የሐዋሪያት 13፡8
 • በተጨማሪም እወንተኛ ክርስቲያኖችንም ጭምር በትምህርታቸው ለማሳት ያላሰለሰ ጥራት ያደርጋሉ።  ማርቆስ 13፡22። ይህም በጳውሎስ ለጢሞቲዮስ በፃፈው መልክቶች  ትክክለኛ እና ጤናማ አስተምህሮ ጥቅሞችን ይገልፃል። 1 ጢሞ 4፡6 ፤2ጢሞ4፡6፥2 ፤2ጢሞ 4፡3 ቲቶ 1፡9፤2፡1

3. በመጨረሻም የሀሰተኛ ነብያት ፍሬዎች መታወቂያ በሚያሳዩት ገፀ ባህርያት እና ጠባይ ነው። በቀላሉ የሚለዩባቸው ገፀባህርያት

 • ትዕብት 2ጴጥሮስ 2፡1
 • ስስትነት ኤርሚያስ 8፡1 ቲቶ 1፡11 2ጵጥሮስ 2፡3፡14
 • ያካሄድ ክፋት ወይም በሃጢአት ልምምዶቻቸው ኤርሚያስ 23፡11፥14፤2ጴጥሮስ 2፡14
 • ስጋዊነት የተጠናወታቸው ናቸው 2 ጴጥሮስ 2፡1 ፥ 12 ፤3፡3
 • በደካምና በጥፋት ውስጥ የሚነዱትን ያድናሉ። 2ጢሞቲዮስ 3፡6-7 ; 2 ጵጥሮስ 2፡14፤13
 • እግዚአብሔር እናውቃለን ይላሉ ነገር ግን በስራቸው ይክዱታል። ማቴዎስ 7፡2-23; 2ጢሞቲዮስ 3፡5 ፥ቲቶ 1፡16
 • ስልጣንን ለስጋቸው ፍቃድ ደስታ ያዉሉታል ደግሞም ለማንም አይታዘዙም 2ጴጥሮስ 2፡10

“ዕውር ዕውርን ሊመራ ይችላልን? ሁለቱ በጕድጓድ አይወድቁምን?” ሉቃስ 6፡39

በሰፊው ጎዳና የሚመሩ ብዙ አምላክ የለሽ መሪዎች አሉ ፍፃሜውም ጥፋት ነው። እነኚ መምህራን ማየት ይማይችሉ  ዕውር ብቻ ሳሆኑ ሌሎችንንም ወደ ጥፋት ይመራሉ። የመጨረሻውን ፍርድ እና ቅጣት የሚሰጣቸው ጌታ እራሱ ነው።

Related Topics: Bible Study Methods, Character Study, Christian Education, Church Discipline, Issues in Church Leadership/Ministry

Report Inappropriate Ad