ምዕራፍ 11።

1፤ የሕዝቡም አለቆች በኢየሩሳሌም ተቀመጡ፤ ከቀሩትም ሕዝብ ከአሥሩ ክፍል አንዱ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፥ ዘጠኙም በሌሎች ከተሞች ይቀመጡ ዘንድ ዕጣ ተጣጣሉ።

2፤ ሕዝቡም በፈቃዳቸው በኢየሩሳሌም ለመቀመጥ የወደዱትን ሰዎች ሁሉ ባረኩ።

3፤ በኢየሩሳሌምም የተቀመጡት የአገሩ አለቆች እነዚህ ናቸው፤ እስራኤል ግን ካህናቱም ሌዋውያኑም ናታኒምም የሰሎሞንም ባሪያዎች ልጆች እያንዳንዳቸው በየርስታቸውና በየከተማቸው በይሁዳ ከተሞች ተቀመጡ።

4፤ ከይሁዳና ከብንያምም ልጆች እነዚህ በኢየሩሳሌም ተቀመጡ። ከይሁዳ ልጆች፤ ከፋሬስ ልጆች የመላልኤል ልጅ የሰፋጥያስ ልጅ የአማርያ ልጅ የዘካርያስ ልጅ የዖዝያ ልጅ አታያ፤

5፤ የሴሎናዊውም ልጅ የዘካርያስ ልጅ የዮያሪብ ልጅ የዓዳያ ልጅ የዖዛያ ልጅ የኮልሖዜ ልጅ የባሮክ ልጅ መዕሤያ።

6፤ በኢየሩሳሌም የተቀመጡት የፋሬስ ልጆች ሁሉ አራት መቶ ስድሳ ስምንት ጽኑዓን ነበሩ።

7፤ የብንያምም ልጆች እነዚህ ናቸው፤ የየሻያ ልጅ የኢቲኤል ልጅ የመዕሤያ ልጅ የቆላያ ልጅ የፈዳያ ልጅ የዮእድ ልጅ የሜሱላም ልጅ ሰሉ።

8፤ ከእርሱም በኋላ ጌቤና ሳላይ ዘጠኝ መቶም ሀያ ስምንት።

9፤ አለቃቸውም የዝክሪ ልጅ ኢዮኤል ነበረ፤ የሐስኑአም ልጅ ይሁዳ በከተማው ላይ ሁለተኛ ነበረ።

10፤ ከካህናቱ፤ የዮያሪብ ልጅ ዮዳኤ፥ ያኪን፥

11፤ የእግዚአብሔርም ቤት አለቃ የአኪጦብ ልጅ የመራዮት ልጅ የሳዶቅ ልጅ የሜሱላም ልጅ የኪልቅያስ ልጅ ሠራያ፥

12፤ የቤቱንም ሥራ የሠሩ ወንድሞቻቸው ስምንት መቶ ሀያ ሁለት፤ የመልክያ ልጅ የፋስኮር ልጅ የዘካርያስ ልጅ የአማሲ ልጅ የፈላልያ ልጅ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፥

13፤ ወንድሞቹም የአባቶቹ ቤቶች አለቆች ሁለት መቶ አርባ ሁለት፤ የኢሜር ልጅ የምሺሌሞት ልጅ የአሕዛይ ልጅ የኤዝርኤል ልጅ አማስያ፥

14፤ ወንድሞቻቸውም መቶ ሀያ ስምንት ጽኑዓን ኃያላን፤ አለቃቸውም የሐግዶሊም ልጅ ዘብድኤል ነበረ።

15፤ ከሌዋውያንም፤ የቡኒ ልጅ የአሳብያ ልጅ የዓዝሪቃም ልጅ የአሱብ ልጅ ሻማያ፤

16፤ ከእግዚአብሔርም ቤት በሜዳ በነበረው ሥራ ላይ የነበሩ የሌዋውያን አለቆች ሳባታይና ዮዛባት፤

17፤ በጸሎትም ጊዜ ምስጋናን የሚቀነቅኑ አለቃው የአሳፍ ልጅ የዘብዲ ልጅ የሚካ ልጅ መታንያ፥ በወንድሞቹም መካከል ሁለተኛ የነበረ በቅበቃር፥ የኤዶታምም ልጅ የጋላል ልጅ የሳሙስ ልጅ አብድያ።

18፤ በቅድስቲቱ ከተማ የነበሩ ሌዋውያን ሁሉ ሁለት መቶ ሰማንያ አራት ነበሩ።

19፤ በሮቹንም የሚጠብቁ በረኞቹ፥ ዓቁብና ጤልሞን ወንድሞቻቸውም፥ መቶ ሰባ ሁለት ነበሩ።

20፤ ከእስራኤልም የቀሩት ከካህናትና ከሌዋውያንም እያንዳንዳቸው በየርስታቸው በይሁዳ ከተሞች ሁሉ ውስጥ ነበሩ።

21፤ ናታኒምም በዖፌል ተቀምጠው ነበር፤ ሲሐና ጊሽጳ በናታኒም ላይ ነበሩ።

22፤ በእግዚአብሔርም ቤት ሥራ ላይ ከነበሩ መዘምራን ከአሳፍ ልጆች ወገን የሚካ ልጅ የመታንያ ልጅ የሐሸብያ ልጅ የባኒ ልጅ ኦዚ በኢየሩሳሌም የሌዋውያን አለቃ ነበረ።

23፤ ስለ እነርሱም የንጉሥ ትእዛዝ ነበረ፤ የመዘምራኑም ሥርዓት ለየዕለቱ የተሠራ ነበረ።

24፤ ከይሁዳም ልጅ ከዛራ ወገን የሜሴዜቤል ልጅ ፈታያ ስለ ሕዝቡ ነገር ሁሉ በንጉሡ አጠገብ ነበረ።

25፤ ስለ መንደሮቹና ስለ እርሾቻቸው፤ ከይሁዳ ልጆች አያሌዎች በቂርያትአርባቅና በመንደሮችዋ፥ በዲቦንና በመንደሮችዋም፥ በይቀብጽኤልና በመንደሮችዋም፥

26፤27፤ በኢያሱ፥ በሞላዳ፥ በቤትጳሌጥ፥ በሐጸርሹዓል፥

28፤ በቤርሳቤህና በመንደሮችዋ፥ በጺቅላግ፥

29፤ በምኮናና በመንደሮችዋ፥ በዓይንሪሞን፥

30፤ በጾርዓ፥ በየርሙት፥ በዛኖዋ በዓዶላም በመንደሮቻቸውም፥ በለኪሶና በእርሻዎችዋ፥ በዓዜቃና በመንደሮችዋ ተቀመጡ። እንዲሁ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ድረስ ሰፈሩ።

31፤ የብንያምም ልጆች ከጌባ ጀምሮ በማክማስ፥ በጋያ፥

32፤ በቤቴልና በመንደሮችዋ፥ በዓናቶት፥ በኖብ፥

33፤34፤ በሐናንያ፥ በሐጾር፥ በራማ፥ በጊቴም፥ በሐዲድ፥

35፤ በስቦይም፥ በንበላት፥ በሎድ፥ በኦኖ፥ በጌሐራሺም ተቀመጡ።

36፤ በይሁዳም ከነበሩ ሌዋውያን አያሌ ክፍሎች ወደ ብንያም ሆኑ።